ስልኮች ለምን 2/3 የካሜራ ሌንስ አስፈለጋቸው ? |ጥቅማቸውስ

አሁን አሁን ላይ በብዙዎቻችን ስልኮች ላይ 2 እንዲሁም 3 የካሜራ ሌንሶች እየተለመዱ ከአንድ በላይ መሆናቸው ምንድነዉ ስራው ጥቅምስ ይኖራቸው ይሆን ብለው አስበው ያቃሉ ?
አስበው የማያዉቁም ከሆነ ሃሳቡንም ምላሹን ዛሬ እንሰጥዎታለን ፤

ፐሮፌሽናል የሚባሉት ዲጂታል ካሜራዎች ምርጥ የተባሉ ፎቶዎችን ለማንሳት የተለያዩ ሌንሶችን ይጠቀማሉ ማለትም አንድ ፕሮፌሽናል ፎቶ አንሺ ዘመናዊ የተባለዉን ካሜራውን ይዞም ቢሆን የተለያዩ ፎቶዎችን ለማንሳት እንድ ሹቱ የተለያዩ ሌንሶች ያስፈልጉታል

• መደበኛ ፎቶን ለማንሳት standard eye ሌንስ ሲጠቀም ነገር ግን
• በርቀት ያለ አካልን zoom አድርጎ ለማንሳት telephoto ሌንስ
• እንዲሁም : ሰፊ አንግልን በአንድ ፎቶ አካቶ ለማንሳት ደግሞ fish eye ሌንስ…. መጠቀም የግድ ይለዋል ይህን ስንል ጥራት ያለዉን ፎቶ ለማንሳት ለእያንዳንዱ የፎቶ ሹት ሃሳብ ትክክለኛ ሌንስ በጥንቃቄ መምረጥ ግድ የለዋል በአንድ ሌንስም ሁሉንም አይነት ፎቶ ማንሳትም የማይታሰብ ነው ምክንያቱም ሁሉም ሌንሶች የተለያ ስራ ስላላቸዉ ለምሳሌ fish eye/ሰፊ አንግልን ሌንስ ተጠቅመን በርቀት ያለን ነገር መቅርጽ ማሰብ ትርፍ ድካም ስለሚሆን፡

ታዲያ ይሄ ከስልኮች ሌንስ ጋር ምን አገናኘው ?

ለረጅም አመታት በስልኮች ላይ አንድ የካሜራ ሌንስ ብቻ የተለመድ ሆኖ ቆይቶል የስልክ ካሜራዎችን ጥራት ለመጨመርም ቢሆን ሜጋ ፒክስል ከመጨመር ዉጪ የስልክ አምራቾች ሌንሶች ላይ ያደረጉት ማሻሻያ አላደረጉም ነበር ፤ በአንድ ሌንስ ደግሞ ፍጹም የተባለ የፎቶ ጥራት ማግኘት እንደማይቻል አይተናል በኋላ ላይ ግን ባለ ሁለት ሌንስ ካሜራዎች በብዛት ገበያዉን መቀላቀል ጀመሩ

በብዛት ሁለ ት ሌንስ ይዘው የሚመረቱት ስልኮች የመጀመርያዉ ሌንስ ስታንዳርድ ሌንስ ወይንም መደበኛ የምንለዉን ፎቶ የሚያነሳ ሲሆን ሁለኛው ሌንስ ደግሞ telephoto ነው ይህም በርቀት ያሉ አካላትን አቅርቦ ለማንሳት አልያም በቅርበት ላሉትም ቢሆን closeup shot በጥራት ለማንሳት የጠቅማል ፤ ታዲያ እዚህ ጋር በባለአንድ ሌንስ ስልኮችስ zoom አርገን ፎቶ ማንሳት እንችል የለወይ የሚልጥያቄ ሊነሳ ይችላል መልሳችን አይቻልም ነው በባለ አንድ ሌንስ ስልክ zoom ስናረግ በትክክል አቅርቦ እያሳየን ሳይሆን አንዴ በሌንሱ የተነሳዉን ፎቶ /ሴንስ ይተደረገውን ምስል አጉልቶ ብቻ ነዉ የሚያሳየን ይህ ደግሞ digital zoom ነው ማለትም ፌክ ነዉ፡፡ ለዚህም መፍትሄ ነው ሁለተኛው ሌንስ 2X የጎላ ምስል የሚያስገባልን፡፡

አንዳንድ እንደ lG ያሉ የስልክ አምራቾች ደሞ ሁለተኛዉን ሌንስ ሰፊ አንግልን ለማንሳት የሚያገለግል fish eye lense ያደርጉታል
ሌሎች አምራቾች ደግሞ አንዱን ሌንስ monochrome/ባለነጭና ጥቁር ቀለም ብቻ የሚያነሳ

ያደርጉትና ሁለተኛዉን ደግሞ ባለቀለም ስታንዳርድ ሌንስ ይሆናል ይሄንንም የሚያደርጉት monochrome ሌንሶች ከባለቀለሞቹ በተሻለ ብርሃንን የመለየት አቅም ስላላቸውና በቂ ብርሃን በሌለበት ቦታ በጥራት ምስልን ማንሳት ስለሚችሉ ነዉ በመቀጠል ስልካችን እነዚህን በተለያየ ሌንሶች የተነሱትን ምስሎች በተራቀቀ ሶፍትዌር አንድ በማድረግ ጥራት ያለው ፎቶ ያስቀርልናል፡፡

ይህ አዲስ የሶፍትዌር አሰራር ሊመስለን ይችላል ነገር ግን ባለ አንድ ሌንስ ስልኮች ላይም HDR ሞድ ስንጠቀም ተመሳሳይን ሂደትን ነዉ ስልካችን የሚጠቀመዉ ልክ ስናነሳ 3 የተለያዩ ፎቶዎችን ያነሳና ስልካችን እነሱን በመቀላቀል ጥራት ያለው አንድ ምስል ያመርትልናል ነገር ግን የምናነሳዉ ምስል እንቅስቃሴ ከሌለው ብቻ ነው HDR የሚሰራው፡፡
ከላይ ስለባለሁለት ሌንስ ካሜራ ስልኮች አይተናል ነገር ግን አሁን ላይ ባለ 3 ሌንሶች ላይም ደርሰናል እነዚህ ደግሞ በብዛት የሚያገለግሉት
የመጀመርያው ሌንስ ለ መደበኛ ፎቶ
ሁለተኛው ደግሞ በርቀት ያሉ አካላትን እንዲሁም በ zoom closeup ምስሎችን ለማንሳት የሚጠቅም ሲሆን
ሶስተኛው monochrome ይሆንና የምስሉን ብርሃን በማመጣጠን ጥራት የሰጠዋል
በብዙ ሳምሰንግ ስልኮች ላይ ደግሞ 3ኛው ሌንስ depth ሌንስ ሆኖ እናገኘዋለን ይሄም ጠቀሜታው ለ live focous ነው ማለትም ከምናነሳው አካል ጀርባ ያሉትን ነገሮች በማፍዘዝ በዋናነት የምናነሳዉን አካል ጎልቶ እንዲታይ ማድረጉ ነው

ስለዚህ የስልኮቻችን ሌንሶች በዚህ አግባብ ለተለያይ ጥቅም እንዲሰጡ ታቅደዉ የተቀመጡ ናቸው ፤ ምናልባትም ባለ4 ሌንስ ካሜራ ስልኮችንም ማየት ጀምረን ይሆናል ፤ ይህም ሰፊ አንግል አጠቃለን በአንድ ምስል እንድ ናነሳበት የተዘጋጀ ነዉ፡፡ ከዚህም በላይ የተራቀቁ የካሜራ ሌንሶች የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም እኛም በሌላ ጦማር እንገናኝለን

Biniyam Abera

IT Consultant , & Chief Technical Officer at Salis Technologies

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: