ስልክዎት ኦሪጅናል መሆኑን ማረጋገጫ መንገዶች!

ስላም ውድ ተከታታዮቻችን፣ በአሁኑ ወቅት የስልክ ዋጋ በጣም እየጨመረ የመጣበት ጊዜ ላይ ነን፣ እንደዛም ሆኖ የገዙት ስልክ ኦርጅናል አይደለም ቢባሉ ኪሳራውን መገመት አይከብድም።

አዲስ ስልክ ሲገዙ እንዳይታለሉ ወይም የያዙትንም ስልክ ኦሪጅናል መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንደሚቻል ቀጥለን እናያለን።

ሶስት ስልክን ኦሪጅናል መሆኑን የምናረጋግጥበት መንገዶች አሉ የመጀመሪያው ለሁሉም ስልክ ሲያገለግል፣ የቀሩት ሁለቱ ለሳምሰንግ ስልኮች ይጠቅማሉ:-

1. በIMEI ቁጥር

ወደ ስልክዎት መደወያ በመግባት ወደ *#06# ይደውሉ።

በመቀጠል የIMEI ቁጥሩን ኮፒ ያድርጉት ወይም ፅፈው ይያዙት

ወደ www.imei.info ይግቡ

Imei

ከገቡም በኋላ ቁጥር ማስገቢያው ቦታ ላይ የIMEI ቁጥርዎትን በማስገባት Check የሚለውን ይጫኑት።

ከተጫኑት በኋላ ዌብሳይቱ ስለ ስልክዎት ሁሉንም መረጃ ይዘረዝርልዎታል። የመጣልዎት ውጤት የኦሪጅናል ስልክን የሚያሳይ ከሆነ ስልክዎት ኦሪጅናል ነው ማለት ነው።

ለሳምሰንግ ስልኮች

ወደ ስልክ መደወያ በማምራት *#0*# ይደውሉ፣ ይህን ሲያደርጉ በአራት ማእዘን ብዙ ምርጫዎች ከመጣልዎት ስልክዎ ኦሪጅናል ነው። እነዚህን ምርጫዎች በመጠቀም የስልክዎን ሃርድዌር መሞከር ይችላሉ።

ወደ ስልክዎት ፕሌይ ስቶር በመግባት Phone Info ብለው ይፈልጉ ወይም እዚህ ተጭነው መተግበሪያውን ያውርዱት።

Phone Info *SAM*

Phone Info *SAM* የሚለውን መተግበሪያ ከከፈቱት በኋላ ወደ ማውጫው በማምራት Refubrish Check የሚለውን ተጭነው ኦሪጅናል መሆኑን ያረጋግጡ።

Bisrat Girma

Co-Founder of Salis Technologies, Software Engineer and Digital Marketer.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: