የፌስቡክ የገቢ ምንጭ ከየት ነው ?

እንደምናቀው ፌስቡክ ስንጠቀም የምስል,የቪዲዮ እንዲሁም የፅሁፍ ማከማቻ ሰቶን ከሌሎች ሰዎች ጋር የምንገናኝበትን ምህዳር ፈጥሮልን የሚያስከፍለን ነገር የለም ማለትም ወጪያችን ለቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት የምናወጣው በይነመረብ/internet ወጪ ብቻ ነው። (ለብዙዎቻችን የሞባይል ካርድ )

ታዲያ ፌስቡክ ገቢውን ከየት ያመጣል ?
ፌስቡክ ዋናው ገቢው ማስታወቂያ ነው። በምስሉ ላይ እንደሚታየው በተደጋጋሚ በ New feeds ላይ sponsored የሚል ልጥፍ አስተውለን ይሆናል። ይህም ማለት ተከፍሎ እኛ ጋር እንዲደርስ የተደረገ ማስታወቂያ ማለት ነው።

ባለንበት ዘመን ብዙ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያና በበይነመረብ ላይ ብዙ ጊዜያቸውን ያጠፋሉ ። ስለዚህም ፌስቡክ ተመራጭ የማስታወቂያ ስፍራ አርጎታል።
ማስታወቂያው ለተመረጡ ተጠቃሚዎች/ target marketing መሰረት አድርጎ የሚሰራ ነው ማለትም የፌስቡክ ተጠቃሚወች መረጃ ለማስታወቂያው ዋነኛ ግብዐት ነው ማለት ነው።

ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የፌስቡክ ማስታወቂያ አገልግሎት የሚሰጡ የማህበራዊ አውታረ መረብ ኤጀንቶች አሉ በሀገራችንም ሳልስ ቴክኖሊጅስን/www.salis3.com የመሳሰሉ የ ዲጅታል ማርኬቲንግ ድርጅቶች ይገኛሉ ።

Biniyam Abera

IT Consultant , & Chief Technical Officer at Salis Technologies

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: