የሀሰት ዜናዎች አና ሳይበር ፕሮፖጋንዳ/በማህበራዊ ሚዲያዎች (ክፍል 2)

ተጽእኖ ፈጣሪ የሀሰት ዜናዎችና ሳይበር ፕሮፖጋንዳ የሚዘጋጁበትን ሂደት በቅደም ተከተል

በዚህ በፊት በነበረዉ ፖስታችን የገለጽናቸዉን ግብአቶች በመጠቀም እንዴት ፕሮፓጋንዳ መፍጠር ማቀጣጠል በመቀጠልም ተጽእኖ መፍጠር እንደሚቻል እንመልከት፤

በዋነኛነት መረጃዎቹን ለማስፋፋትና ለማሰራጨት አንድ አክቲቭ ተዋናይ ያስፈልገናል ፤ የሚገዙ follows/fans , like , repost , comment ይኖራሉ ነገር ግን እነዚህን ለመግዛት ብዙ የገንዘብ ፈሰስ ማድረግ ይጠበቅብን ይሆናል ፤የብሩ መጠን በጨመረ ቁጥር ጥራታቸዉ ስለሚጨምር የግዢ መሆናቸዉን ለመለየት ደግሞ ያዳግታል፤ፈሰስ የሚደረገዉ ገንዘብ በኋላ ላይ ከሚያስገኘዉ ትርፍ አንጻር የሚወሰን ነዉ፡፡ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲሆን ደግሞ የሚወጣዉ ገንዘብ የትየለሌ ይሆናል፡፡

[ምስሎቹን በቅደም ተከተል ተመልክተዉ ይመለሱ]

በስተመጨረሻ መወሰድ ያለበት እርምጃ ብለን ያሰብነዉን እንዲህ አስቀምጠነዋል ፤ ግለሰቦች፣ድርጅቶችም እንዲሁም መንግስት የሃሰት ዜናዎች የሚፈጥሩትን አሉታዊ ተጽእኖ ተገንዝበን ፡፡ ግለሰቦች የእነዚህ ሀሰተኞች ሰለባ እንዳንሆን መንቃት ፤ መንግስትም ደግሞ እነዚህን የሚያሰራጩትን ሚዲያዎች ግለሰቦች ተጠያቂ የሚሆኑበትን ህግ ማርቀቅ ይህን ስንል መንግስት ራሱ የሳይበር ፕሮፓጋንዳ እንደሚጠቀም ዘንግተነዉ አይደለም፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ አቅራቢዎችም የሀሰት ዜናዎች ጉዳት ከመፍጠራቸዉ በፊት በፍጥነት የሚነሱበትና ሪፖርት የሚደረጉበት መንገድ ቢቀረጽ እንላለን ፡፡


ከ አሳሳች ዜና ተጠበቁ የዛሬ መልክታችን ነዉ

Biniyam Abera

IT Consultant , & Chief Technical Officer at Salis Technologies

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: