የኢንስታግራም ማስታወቂያ

የኢንስታግራም ማስታወቂያ ለብዙ እና የተመረጡ የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ጋር ለመድረስ ተደርጎ እንደ አንድ የኢንስታግራም ልጥፍ አይነት ሆኖ በክፍያ የማስተዋወቅ ዘዴ ነው።

ኢንስታግራም የፎቶ(Visual) እና የቪድዮ መድረክ እንደመሆኑ፣ የፅሁፍ ማስታወቂያዎች ቦታ የላቸውም። ይልቁንስ በኢንስታግራም ማስታወቂያዎች አዲስ ደንበኛዎት ጋር ለመድረስ ምስል፣ የምስል ስብስብ ወይም ቪድዮ ያስፈልግዎታል።

ለእርስዎ ንግድ የኢንስታግራም ማስታወቂያ ትክክለኛው ነው?

ይህ ጥያቄ ኢንስታግራምን ማነው የሚጠቀመው ወደሚለው ይመራናል። ኢንስታግራምን የሚጠቀሙት አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው።
ከሙሉ ተጠቃሚ ውስጥ 55% የሚሆኑት ከ18-29 ባለው ዕድሜ ላይ ይገኛሉ፣ ከ30-49 ያሉት ደግሞ 28% ተጠቃሚውን ይይዛሉ። ቀሪዎቹ ደግሞ ከ13 አመት በላይ የሆኑ ታዳጊዎች እና ከ50 አመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ያጠቃልላል።

እርስዎ አዋቂዎችን ያማከለ ንግድ ላይ ያተኮሩ ከሆነ፣ አያሳስብዎ 15% ለሚሆኑት ከ 50 አመት እድሜ በላይ ላሉት ለይተው ማስተዋወቅ ይችላሉ።

እንደ ሌሎች የማህበራዎ ትስስር የማስታወቂያ መንገዶች፣ ኢንስታግራምም ተጠቃሚዎቹን በፆታ፣ በዕድሜ፣ በቦታ፣ በፍላጎት፣ በባህሪ እና በተለያዩ ለይታችሁ ለተጠቃሚዎች እንድታስተዋውቁ እድል ይሰጣል።

ምን ያህል ያስከፍልዎታል?

የኢንስታግራም ማስታወቂያዎች ከአባት ድርጅቱ ፌስቡክ ውጤታማነታቸው ላቅ ያለ ስለሆነ፣ የሚያስከፍለውም ከፌስቡክ ማስታወቂያ በትንሹ ይጨምራል።

የማስታወቂያዎቹ አይነቶች

የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ቋት(Instagram Users Feed) ላይ በምስል የሚደረግ ማስታወቂያ


ምስልን በመጠቀም የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ታሪክ(Story) የሚለቀቅበት መሃል ላይ ማስተዋወቅ


የምስል ስብስብ(Carousel) ማስታወቂያ


የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ቋት(Instagram Users Feed) ላይ በቪድዮ የሚደረግ ማስታወቂያ


ውጤታማነቱ

ኢንስታግራም ላይ ቀጥታ ማስተዋወቅ ይቻላል ከአርስዎ የሚጠበቀው የፌስቡክ መክፈያ መንገዶችን መጠቀም መቻል ነው፣ ነገር ግን ውጤታማነቱ ላይ እርግጠኛ መሆን ኣይቻልም(ROI)። ስለዚህ ከዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያ ጋር አንድ ላይ ስራቱ ይመረጣል።

Bisrat Girma

Co-Founder of Salis Technologies, Software Engineer and Digital Marketer.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: