የሀሰት ዜናዎች አና ሳይበር ፕሮፖጋንዳ/በማህበራዊ ሚዲያዎች

አሁን ባለንበት ወቅት የሀሰት ዜናዎች እና መረጃዎች በስፋት በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተስፋፋ/እየተሰራጨ እኛም ተቀብለን እያዳረስነዉ እንገኛለን ታዲያ ይህ የሀሰት ዜና ብዙ መዘዞችን ይዞ መምጣቱ አይቀሬ ነዉ፤ ስለሀሰት ዜናዎች ካለን ግንዛቤ ተያይዞ የተፈጠረ ስለመሰለን ስለ ሳይበር ፕሮፓጋንዳ እንደዚህ አቅርበናል ፡፡


የሀሰት ዜናዎች የሚለዉን ቃል ስንሰማ በቅድምያ ወደ ጭንቅላታችን የሚመጣዉ በፌስቡክና በማህበራዊ ሚድያ የሚለቀቁትን ተአማኒነት ያሌላቸዉን እና አስደናቂ ታሪኮችን ነዉ ፤ ማህበራዊ ሚዲያ በብዙ ሰዎች ያለዉን ተደራሽነቱን በመጠቀም የሀሰት ዜናዎችና እጅጉን የተጋነኑ አንቀጾችን ቀልብን ከሚስቡ ርእሶች ጋር ይቀርባሉ ፡፡

የሀሰት ዜናዎችና ሳይበር ፕሮፖጋንዳ
የሀሰት ዜናዎች ሲባል ከላይ እንደጠቀስነዉ ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር ብቻ አያይዘን ልንመለከተዉ እንችላለን ነገር ግን ፕሮፓጋንዳዉ ሳይሆን አዲሱ ነገር ፤ በማህበራዊ ሚዲያ መለቀቁና የሚተላለፉበትን ምህዳር/platform መቀየሩ ነዉ አዲስ ፤ፕሮፖጋንዳ ለዘመናት አልፎም ለክፍለ ዘመናት የቆየ ሲሆን በየነ-መረብ/internet ደግሞ ዘመናዊው የመገናኛ እና የመረጃ መለዋወጫ መንገድ እንደመሆኑ ዉሸቶች እና የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ የፕሮፓጋንዳ እና የዲስኩር መተግበርያ አድርገነዋል ፡፡

እሳትን ለማቀጣጠል 3 መሰረታዊ አካላት/elements ያስፈልጋሉ እነዚህም አየር/oxygen , ሙቀት , ነዳጅ ናቸዉ በተመመሳሳይ መልኩ የ ሳይበር ፕሮፓጋንዳን ለማቀጣጠል 3 መሰረታዊ ነገሮች ያስፈልጋሉ ፡፡
1, ማህበራዊ ሚዲያ/አዉታረ መረብ
2, አነሳሽ ምክንያቶች
3, መሳርያዎች፤አገልግሎቶች/services

መሳርያዎች እና አግልግሎቶች ስንል አጭበርብረን ተአማኒነት ለማግኘት እንዲሁም የሀሰት ዜናዎችን በሰፊው በማህበራዊ አዉታረመረቦች ላይ ለማዳረስ የምንጠቀምባቸዉ አገልግሎቶች/tools ናቸዉ ፡፡ እነዚህም በቀላሉ በ በየነመረብ ላይ ከየትኛውም ቦታ ላይ ሆነን ልንገዛቸዉ እና ልንጠቀምባቸዉ እንችላለን ፤ ተደራሽነትና ለመጨመር ብዙ አይነት መሳርያዎች ቢኖሩም ለምሳሌ ያክል፦ በክፍያ ተከታዮችና የገጽ like ማብዛት ፣ቡስት ፖስትን በመጠቀም ልጥፎችን በቀን በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ማድረስ ወዘተ

እርግጥ ነዉ የሃሰት ዜናዎችን ሀሰትነታቸዉን ከተረጋገጠ የድህረገጹ አስተዳዳሪዎች ከገጻቸዉ ላይ በግድም ቢሆን የሀሰት መረጃዎቹን ሊያስጠፋቸዉ ይችላሉ፤ነገር ግን እነዚሁ መረጃዎች በሌሎች አማራጭ ሚዲያዎች መቅረባቸዉ አይቀሬ ነዉ፤በዚህ ዘመን ላይ ደግሞ አብዛኞቻችን ረጅሙን ሰአታችንን በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነዉ የምናጠፋዉ ፤የዜና እና የመረጃ ምንጭ አድርገን የምንጠቀመዉ እነዚሁን ማህበራዊ አዉታረመረቦች ነዉ ለዚህም ይመስላል በነዚህ ላይ የሚሰራዉ ፕሮፓጋንዳ ትልቅ ተጽእኖ የሚፈጥሩት ፤

ሌላዉ ነገር ደግሞ በቀላሉ እነዚህን ዜናዎች በቀላሉ እነዚህን መለጠፍ/መልቀቅ ብቻ ሳይሆን የተፈለገበት ታዳሚ ጋር በመድረስ የውሸቱንና የፕሮፓጋንዳዉ ተጽእኖ ሰለባ ያደርጉታል ለዚህም ነዉ አጭበርባሪዎች ምን አይነት ቴክኒክ ተጠቅመዉ ታሪኮቻቸዉን እንድንመለከት እንደሚያደርጉን መረዳት የሚኖርብን፤ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰሩበትን መንገድ ስናጤነዉና ስንመለከተዉ የማህበራዊ አዉታረ መረቦች ማስታወቂያ እና ቦቶች/bots ለድርጅት ማስታወቂያ ቅስቀሳ እንዲያገለግሉ ታቅደዉ ቢቀረጹም የህዝብን እይታ በቀላሉ እንዴት እንደሚቀይሩ ማስተዋል ይቻላል፡፡

በስተመጨረሻም የሳይበር ፕሮፓጋንዳ እና ዲስኩር ቅስቀሳዎች ለምን አላማ ነዉ የሚዉሉት ? አነሳሽ ምክንያቶች ስናይ አንደኛዉ የገንዘብ ተጠቃሚነትን ለመጨመር ከቢዝነስ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘ ሲሆን በሌላኛዉ ጽንፍ ደግሞ በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደምናስተዉለዉ የፖለቲካ የበላይነትን የፖለቲካ ትርፍን ለማግኘት ተብሎ የሚሰራ ነዉ ፤ የሳይበር ፕሮፓጋንዳ ስኬት የሚለካዉ በትክክል መሬት ላይ በፈጠረዉ ተጸእኖ/impact ልክ ነዉ፡፡

(ተጽእኖ ፈጣሪ የሀሰት ዜናዎችና ሳይበር ፕሮፖጋንዳ የሚዘጋጁበትን ሂደት በቅደም ተከተል
ይቀጥላል…..)

Biniyam Abera

IT Consultant , & Chief Technical Officer at Salis Technologies

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: