የፌስቡክ ማስታወቂያ ጠቀሜታቸው

የፌስቡክ ማስታወቂያ ዋና ጠቀሜታው ተፈላጊዉን ታዳሚ/audience/ ጋር ብቻ መድረሱ ነዉ፤
ማለትም
በምሳሌ ስንመለከትአንድን የቢራ ማስታወቂያ ከ 21 -50 አመት ለሆኑ ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ማቅረብ ከሆነ የተፈለገዉ ፤ በልዩነት ለእነሱ ብቻ ይቀርባል እንጂ ማስታወቅያዉ አላስፈላጊ ወይንም ያልታቀደበት ቦታ ላይ አይታይም ይህ መሆኑ የማስታወቂያዉን እምርታ ይጨምረዋል፡፡

የፌስቡክ ማስታወቂያ ታዳሚዉን የሚለየዉ ከላይ እንደተገለጸዉ ምሳሌ የቦታና የእድሜ መለያ ተጠቅሞ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተጨማሪ መንገዶችን በመጠቀም ነው፣ ማለትም የ ፌስቡክ ተጠቃሚዉን ማህደር በማጥናት የግለሰቡን ፍላጎትም ከግምት ዉስጥ በማስገባት የሚሰራ ነዉ፡፡ በፌስቡክ ላይ ማስታወቂያ መስራት/ማሰተዋወቅ ሰፊ ጠቀሜታ ያለዉ ሲሆን ጥቂቶቹን ስንመለከት ፦

  1.  በአሁኑ ሰአት ፌስቡክ በርካታ ተጠቃሚዎች ስላሉት ፡ ሰፊ ተደራሽነት ስለሚሰጥ
  2. ካሉት የማስታወቂያ አይነቶች ጋር ሲነጻጸር ርካሽ መሆኑ
  3.  የንግድ ስም/ምልክትን በሰፊው ለማስተዋወቅ
  4.  ማስታወቂያዉ ለታዳሚዉ በፍጥነት መድረሱ
  5.  ድህረ ገጽ ካለን የድህረ ገጽ ጎብኛችንን ስለሚጨምር
  6. በማስታወቂያዉ የሚገኙ ዉጤቶች እንዲሁም የማስታወቂያውን ጥራት በስታቲክስ መግለጽ መቻሉ
  7.  ከተጠቃሚዎች ጋር ከአንድ ጊዜ በላይ የሆነ ደንበኝነት መፍጠሩ
  8. የደንበኞቻችን content/አድራሻ ለመያዝ ስለሚረዳ እና

ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት..

Biniyam Abera

IT Consultant , & Chief Technical Officer at Salis Technologies

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: