የድህረ-ገፅ ስም ማሳጠርያ /web wrapper
የድህረ-ገፅ ስም ማሳጠርያ
web wrapper/ዌብ ራፐር ምንድነው ?
ራፐር ማለት: የአንድ ነገር መጠቅለያ ወይንም መሸፈኛ አሊያም መደበቂያ ነው።
ታዲያ ዌብራፐር (webwrapper) ማለትስ?
ይህን ወደ web/ድህረ-ገጽ መለያ ስም (domain name) አምጥተን ስንመለከተው የአንድን ድህረ ገፅ ስሙን በመሸፈን/በመደበቅ አልያም አሳጥረን የምናስቀምጥበት መንገድ ነው።
ከሚታወቀው ድህረ-ገጽ (domain name) በተለየ በአጭር ቁጥር እና ፊደሎች link/ሊንክ ልናስቀምጥ እንችላለን ማለት ነው።
ይህንንም ደግሞ በማሳጠር አገልግሎት የሚሰጠን አገልግሎት ሰጪ web apps/ ድህረገጾች አሉ። እነዚህም ከነሚጠቀሙት መለያ ጋር በምስሉ ላይ ይታያሉ።