እንዴት በሲቢኢ(CBE Birr) የመብራት እና የውሃ ቢል መክፈል ይቻላል?

የዲጂታል ክፍያዎች ህይወትን ለማቅለል ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። በዚህ ወቅት በተፈጠረው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት እራስዎን ለበሽታው ተጋላጭ ላለማረግ ህዝብ የሚበዛባቸውን ቦታዋች ባያዘወትሩ ይመረጣል፣ የውሃ እና የመብራት ክፍያዎች የህዝብን ተጋላጭነት ከሚጨምሩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተወሰኑት ናቸው። ስለዚህ እራስዎትን ጠብቀው በቤትዎ ሆነው እንዴት የመብራት እና የውሃ ቢሎችን እንዴት መክፈል እንደምንችል እናያለን።

የውሃ መክፈያ short code ቁጥር 878787
የመብራት መክፈያ short code ቁጥር 707070
ስልክዎ ስማርት ፎን(Android) ከሆነ ይሄን ተጭነው ከፕሌይ ስቶር(Play Store) ላይ ያውርዱት!

የውሃ ቢል በሲቢኢ ብር መክፈል
1. ወደ ሲቢኢ ብር *847# መደወል

ወደ ሲቢኢ ብር ደውለው ከሚመጣልዎት ምርጫ ላይ Pay Bill ወይም ቢል ክፈል የሚለውን እንመርጣለን።

CBE BIRR FIRST PAGE
CBE BIRR LIST OF SERVICES

በመቀጠልም ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ Input Short Code ወይም የክፍያ መለያ ቁጥር የሚለውን ይመርጣሉ።

ከመረጡም በኋላ የወሃ እና ፍሳሽ ኮድ የሆነወን 878787 ያስገባሉ።

በመጨረሻም የቢል ቁጥርዎን በማስገባት፣ ገንዘቡን በማረጋገጥ መክፈል ይቻላል።

2. የሲቢኢ አፕልኬሽን በመጠቀም

የሲቢኢ አኘልኬሽን ላይ በስልክ ቁጥራችን ከገባን በኋላ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች ላይ pay bill የሚለውን እንመርጣለን።

በመቀጠል Biller short code ላይ 878787 ከዚያም Bill Reference Number ላይ የቢል ቁጥሩን በማስገባት የቆጠረብዎትን ገንዘብ በመመልከት መክፈል ይችላሉ።

በተጨማሪም ሲቢኢ ብርን(CBE Birr) የመብራት አገልግሎት ክፍያን ለመክፈል ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

Bisrat Girma

Co-Founder of Salis Technologies, Software Engineer and Digital Marketer.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: