የንግድ ፌስቡክ ገፅ አከፋፈት

ፌስቡክ በአሁኑ ሰዓት ከ 2.2 ቢልየን በላይ የሚሆኑ የወር ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት፤ በኢትዮጵያ ደሞ 6 ሚልዮን የሚሆኑ። ንግድ ላይ እንዳለ ሰው ፌስቡክ የሚፈልጉት ደንበኞቾ ጋር ለመድረስ የሚያስችልዮ ትልቅ እድል ነው።

የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ብዛት በኢትዮጵያ

ጥሩ፣ ስለዚህ ከየት እንጀምር? ወይም ቀለል ያለ መንገድ ይገኛል?

እነዚህን 5 ቀላል መንገዶች በመከተል የንግድ ገፁን ሊያገኙት ይችላሉ።

1. ንግድዎን የሚገልፁ ፎርሞችን መሙላት

ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ተጭነው የፌስቡክ ፔጅ መክፈቻ ገፅ ላይ ይግቡ

https://www.facebook.com/pages/creation/

ልክ እዚያው ፔጅ ውስጥ እንደገባቹ ከታች ያለውን ምስል አይነት ምርጫ ታገኛላቹ።

create page ethiopia

ፔጁን የምንከፍተው ለንግድ ስለሆነ፣ ካለው ምርጫ ውስጥ ቢዝነስ ወይም ብራንድ(Business or Brand) የሚለውን እንመርጣለን።

ቀጥሎም ለንግዳችን ስም እና ምድብ(category) እንሰጠዋለን። አንዴ ለንግድዎ ስም ከሰጡት መቀየር እንደማይቻል ያስታውሱ።

2. የመገለጫ ምስል(profile picture) እና የሽፋን ምስል(cover photo) ያስገቡለት

ለንግዳችን ስም ሰጥተነው ካበቃን በኋላ ፌስቡክ እራሱ የመገለጫ ምስል(profile picture) እንድናስገባበት የመራን ቦታ ላይ፣ የንግዳችን ሎጎ እናስገባለን። የመገለጫ ምስሉም ጎኑ እና ርዝመቱ እኩል ቢሆን ይመረጣል፤ በተጨማሪ የሽፋን ምስልዎ ደግሞ ጎኑ ረዘም ያለ ማለትም በትንሹ 820 pixels ሰፊ እና 312 pixels ርዝመት እንዲኖረው ይፈለጋል።

3. የፔጆትን መረጃ እንዳለ ያስገቡ

የንግድዎን ፎቶ ካስገቡ በኋላ ፌስቡክ ወደ አዲሱ ገፆት ይመራዎታል፤ ቀጥለውም ስለ(About) የሚለውን ቦታ ይምረጡት።

Facebook About

ቀጥሎ ከዩዘርኔም(user name) ጀምሮ እስከ መጨረሻ ድረስ ያሉትን መረጃዎች ያስገቡ

ለምሳሌ፦

  • ከደንበኞቻቹ ጋር የሚያገናኗቹ መረጃዎች(Contact Information)
  • ማብራሪያ(Description)
  • ቦታ(location) … ያስገቡ።

4. ተባባሪዎችን ፔጆት ላይ ማካተት

የፌስቡክ ማርኬቲንግ ስራዎችን ለሌሎች ማጋራትን ከመረጡ፣ ለተለያዩ ባለሙያዎች ወይም ሰራተኞቾ ድርሻዎችን መስጠት ይኖርቦታል።

ፌስቡክ ያስቀመጣቸው ሚናዎችን እንይ

  • አድሚን ፦ ሁሉንም ነገር ሙሉ ለሙሉ የሚቆጣጠር( ፔጁን ሲከፍቱት እርስዎ አድሚን ሆነው ነው የሚጀምረው)
  • ኤዲተር፦ ፔጁን ማስተካከል ይችላል፣ ሚሴጅ መላክ ይችላል እና እንደ ፔጁ ፖስት ማረግ ይችላል፣ ማስታወቂያዎችን መፍጠር ይቻላል እና ሌሎችም
  • ሞደሬተር፦ መልዕክት መላክ ይችላል፣ ኮሜንት ማረግ ይችላል፣ ኮሜንት መደለት ይችላል፣ ማስታወቂያዎችን መፍጠር እና ኢንሳይቶቾን ማየት ይችላል።
  • አድቨርታይዘር፦ ማስታወቂያዎችን መፍጠር እና ኢንሳይቶችን ማየት ይችላል።
  • አናሊስት፦ ኢንሳይቶችን ማየት ይችላል።

ለተባባሪዎች(Collaborators) ሚና ለመስጠት፣ ወደ ማስተካከያ(Setting) ሄደው የገፅ ሚና(Page Roles) የሚለው ምርጫ ውስጥ ገብተው ጓደኛዎትን፣ ገጹን ላይክ ያደረጉ ሰዎችን ወይም ኢሜል አድራሻ አስገብተው ለተባባሪዎ ሚና መስጠት ይችላሉ።

5. የመጀመሪያ ፖስቶን መለጠፍ

creating first post

ዋናዎቹን ነገር አስተካክለን ጨርሰናል ግን ገፆት ላይ ተጠቃሚ ሲመጣ የሆነ ነገር ማግኘት አለበት፣ ስለዚህ ገፆት ላይ ለሚመጡት ሰዎች የመጀመሪያ ሊንክ፣ ምስል፣ ቪድዮ ወይም ኢቨንት በማጋራት ገፆን ለሚያዩት ሰዎች መልዕክት ማስተላለፍ ይኖርቦታል።

በነገራችን ላይ ሳልስ ቴክኖሎጂስ የፌስቡክ ገፆትን እንድታስተዋውቁ፣ ተመልካች ወይም ጎብኚ እንዲበዛሎት፣ላይክ እና ሼር እንዲበዛሎት ይረዳዎታል።

Bisrat Girma

Co-Founder of Salis Technologies, Software Engineer and Digital Marketer.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: