3 ስልክዎ ብር እንዳይበላዎት ማረግያ መንገዶች ለአንድሮይድ

በቅርብ ጊዜያት የምንጠቀማቸው ስልኮች ከምንጊዜውም በላይ የዳታ ፍላጎታቸው እየጨመረ፥ እኛንም የበለጠ ገንዘብ እያስወጡን እንደሆነ ይታወቃል። ዛሬ ይህንን እንዴት ማስቀረት እንደምንችል በሰፊው እናያለን። እስከመጨረሻው ተከታተሉን።

3 ምርጥ ስልክዎ ብር እንዳይበላዎት ማረግያ መንገዶች ለአንድሮይድ

1፡ በAndroid Setting ውስጥ የData አጠቃቀሞን ይገድቡ

ይህ Setting በቀላሉ ስልክዎ በወር ከእርሶ ፈቃድ ውጪ ከተፈቀደለት በላይ እንዳይጠቀም ያደርገዋል። ይህንንም የ Android Setting ውስጥ በመግባት ከዛም Data Usage 》Billing cycle 〉Data Limint and billing cycle ውስጥ ገብተው በወር የሚጠቀሙትን ትልቁን የData(ውሂብ) መጠን በማስገባት የስልኮን የወር አጠቃቀም መገደብ ይችላሉ። በተጨማሪም የገደቡት መጠን ላይ ሲደርስ ስልክዎ የData Connectionኑን እንዲያጠፋውም ማረግ ይችላሉ።

2፡ Restrict  App Background data

አንድ አንድ Apps(መተግበሪያዎች)ስልኮን በማይጠቀሙበት ጊዜ ሁላ Data መጠቀማቸውን አያቆሙም። Background Data የስልክዎ ስክሪን ከጠፋ በኋላ የውሂብ አጠቃቀምን ለማስጠካከል ይረዳናል።

ለመጠቀምም Setting 〉〉 Data usage

Restrict ማረግ የሚፈልጉት app ላይ ተጭነው〉 Restict app background data የሚለውን በማብራት የጀርባውን የውሂብ አጠቃቀም መገደብ ይችላሉ።

3፡ ጥራትን መቀነስ

ቪድዮ ወይም ሙዚቃ ኦንላይን የሚያዩ ወይም የሚያዳምጡ ከሆነ የሞባይል Data በሚጠቀሙበት ጊዜ Qualityውን በመቀነስ አጠቃቀሞን መቆጠብ ይችላሉ። ይህንንም በሚጠቀሞቸው መተግበሪያ Setting ውስጥ ያገኞቸዋል። በተጨማሪም የፌስቡክ ዳታ አጠቃቀሞን facebook setting ውስጥ በመግባት Less በማድረግ እንዲሁም ዩቲውብ የሚያቻውቱበትን Resolution በመቀነስ የሞባይል ዳታዎን መቆጠብ ይችላሉ።

https://yetechmkr.bbandf.net/blog/2019/04/25/yetech-mkr-%e1%8b%a8%e1%89%b4%e1%8a%ad%e1%8a%96%e1%88%8e%e1%8c%82-%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%88%ad/

ጉርሻ:ማወቅ እና ማረግ ያለብዎት

  • ትልልቅ ፋይሎችን በዋይ ፋይ ያውርዱ።
  • ሞብይል ዳታዎን አስፈላጊ ካልሆነ ያጥፉት።

Bisrat Girma

Co-Founder of Salis Technologies, Software Engineer and Digital Marketer.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: